”የጪጩ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ማንጀሜንት አባላት ከኦዳ ያኣ ጤና ጣቢያ የልምድ ልዉዉጥ አድሪጎዋል”

by

in

ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም
ዲላ

የጪጩ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከአቻው ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አጠቃላይ የማናጅሜንት አስራር በተመለከተ እንድሁም የጤና ጣቢያው ውስጥ ያሉ ምርጥ ተሞክሮ ለመቅሰም እና ለመማር ሁሉንም የማኔጅመንት አባላት የያዘ ቡድን በኦዳ ያኣ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ተገኝተዋል።

ተሳታፊዎች ኦዳያኦ ጤና  ጣቢያ  ብዙ መልካም ተሞክሮዎችን አግኝተናል ያሉ ስሆን መከባበርን፣ መደማመጥን አብሮ መስራትን እንድሁም ችግሮች ስያጋጥሙ እዛው ምፈቱበተን መልካም ስራዎችን አይተናል  በቀጣይነት ያለንን የአቻነት ወዳጅነት በማጠናከር የጪጩ ጤና ጣቢያንም ወዴ አቻ ተቋም ማንሰራራት እንዳለብን የተገነዘብነው እና ብዙ የቤት ስራዎች እንዳለብን የምያሳይ ጉብኝት ነበር ስሉ ገልፀዋል።

በቆይታቸው ብዙ መልካም ነገር እንደቀሰሙ የተናገሩት የጪጩ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ስዩም ገላግለ አክለው ይህንኑ ልምድ ልውውጥ በተቋማቸው ተግባራዊ እንዳረጋለን ብለዎል።


Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *