የኦዳ ያኣ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ week 3 EOC and RRT ግምገማ አካሂደዋል።

by

in

ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም

የኦዳ ያኣ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ጤና ኤክስቴንሽን እንድሁም ጤና ባለሙያዎች በተገኙበት የ3 ተኛ ሳምንት EOC እና RRT ተገምግሟል በግምገማው መቀናጀት ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ተሳታፊዎች የተለያዩ ተግባራት በጋራ እየከወኑ ይገኛሉ።

በውይይት ወክት በተለይ በ90 ቀናት በታቀዱ ተግባራት ልዩ ትኩረት በመስጠት የወባ በሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ፣የከረምት በጎ ተግባራት ጤና ትምህርት ለህብረተሰቡ መስጠት ፣ የኤችአይቪ ምሪመራ እና ምክር እንድሁም የአጥብ እና እርጉዝ እናቶች ፎረም ማካሄድ ..ወዘተ ተግባር እየተካሄደ ይገኛል።

የጤና ጣቢያው ኃላፊ አቶ አቤነዘር ሰለሞን ተግባራት አቀናጅቶ በመሥራት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኦዳ ያኣ ጤና ጣቢያው ኃላፊ  ከዘርፍ አስተባባርዎች ጋር የ2018 በጀት አመት የውጤት ተኮር እቅድ ስምምነት  ተፈራረሙ ።

የጤና ጣቢያው ሁሉም ስራ ሂደት የ2018 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር እቅድ ስምምነት  ከቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ጋር ተፈራርመዋል።

የውጤት ተኮር እቅዱ በጤናው ዘርፍ ጥራቱን የጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ፓኬጅ በመስጠት እና በመቆጣጠር የህዝቡን ጤና ደህንነት መጠበቅ ነው።

የኦዳ ያኣ ጤና ጣቢያው የጤናውን ዘርፍ ለመለወጥ እና የዜጎችን ጤና ለማሻሻል፣ ጤናን የማበልጸግ፣ በሽታዎችን የመከላከል እና የፈውስ ህክምና ላይ በማተኮር በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል።

በጤና ጣቢያው በጤናው ዘርፍ ለተመዘገቡት ውጤቶች የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ የላቀ ሚናና ለጤና ስርዓቱም መሠረት መሆኑ ተመላክቷል።

በበጀት ዓመቱ የእናቶች፣ ህጻናት፣ አፍላ ወጣቶች ጤና እና ስነ-ምግብ ማሻሻል፤ የበሽታዎች መከላከል እና ጤናን ለማጎልበት በትኩረት እንደሚሰራም ተገልጿል።

የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ በማሻሻል፣ ጥራት ያለው እና ፍትሐዊ የህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት፤ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር እና መልሶ በማቋቋም የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተመላክቷል።

የውጤት ተኮር እቅዱን የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ፣ ህክምና አገልግሎት፣ የጤና ሰው  ሃብት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊዎች ናቸው የተፈራረሙት።

መስሎች ተያይዘዋል ይመልከቱ እና ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ 


Comments

One response to “የኦዳ ያኣ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ week 3 EOC and RRT ግምገማ አካሂደዋል።”

  1. አማን Avatar
    አማን

    አሪፍ በርቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *